በወራት ቢሆንም የእድሜ gapአችን እንደታናሼ እሳሳላታለው በፊት በአይን ባውቃትም አብረን መኖር የጀመርነው በዚህ አመት ነው
እንደ እህቴ ተቀበልኳት ተጣልተን ተኳርፈን እናውቃለን ግን አንድ ቤት ሲኖር ያለ ነገር ነው ብዬ እሷን አረጋጋታለው ብዙ ጊዜ እኔ ቀድሜ ይቅርታ እላታለው በጣም ነው የምሳሳላት በብዙ ነገር እሷን ለማስደሰት ሞክራለው በአንዳንድ ነገሮች ሳልከፋ ቀርቼ አይደለም ግን ቢያንስ እኔ የመከፋቷ ምክንያት መሆን አልፈልግም በዛላይ ይሄን አመት ነው አብሬያት የምሆነው አስከፍቻት መለያየት አልፈልግም
እየቆየሁ ግን ከማያቸው ነገሮች ለኔ ግድ አይሰጣትም እንዴ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ በጣም ለማስደሰት ሳረግ የነበረውን ገደብ ሰጠሁት.....ሲደጋገም ቆረጥኩኝና የራሴን ነገሮች ማድረግ ስጀምር ይቅርታ አለችኝ እንደገና ሰላም ፈጠርን በመቁረጤ መልሼ ራሴን ወቀስኩት
አሁን ላይ ደግሞ ድንገት ከአንቺ ጋር መነጋገር አልፈልግም አለችኝ ....ሲከፋት እንደዚህ ትሆናለች ግን ባሁኑ ያስደነግጣል
በጣም በሰዎች ተለምደናል ብቻዬን ስወጣ ስገባ ይጠይቁኛል ብዙ ነገሮች አብሬ ለምጃለሁ
ምን ላድርግ? በፊት ላይ ቆርጬ ይቅርታ ብላኝ እንደበፊቱ ሁኛለሁ አሁን ደግሞ እኔ ከልቤ ስሆን እንደገና አልፈልግም አለችኝ
ልቁረጥ ? ወይስ ማስተካከል ምችልበት መንገድ ካለ?